ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 13
ጥቅምት ፲፫
- ፲፯፻ ዓ/ም - በታላቋ ብሪታንያ፣ እንግሊዝ እና ስኮትላንድ በሕጋዊ ስምምነት ከተዋሐዱ በኋላ፣ የመጀመሪያው የሕዝብ ተወካዮች ሸንጎ ስብሰባ ተካሄደ።
- ፲፱፻፬ ዓ/ም - በቱርክና በኢጣሊያ መካከል በነበረው ጦርነት የቱርኮችን የጦር ግንባር ከአየር ለመሰለል የኢጣልያ አውሮፕላን ከሊቢያ ተነሳ። ይሄም ድርጊት አውሮፕላን በጦርነት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለበት ዕለት ነው።
- ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - ፔሌ በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው የብራዚል እግር ኳስ ተጫውች ኤዲሶን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ ተወለደ። ፔሌ በዓለም የኦሊምፒክ ሸምቡድ (International Olympic Committee) “የ፳ኛው ክፍለ ዘመን አትሌት” ብሎታል።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የእስራኤልን መንግሥት ሕጋዊነት እንደሚያውቅና እንደሚያከብር ይፋ አደረገ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ከእስራኤል መንግሥት ጋር የነበረውን የ’ዲፕሎማቲክ’ ግንኙነት አቋረጠ።