ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/የካቲት 30
- ፲፰፻፹፩ ዓ/ም - በሱዳን ግዛት ውስጥ ባለችው ገላባት ላይ በዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ የሚመራው የኢትዮጵያ ሠራዊት እና የሱዳን 'ማህዲ' ሠራዊቶች በዚህ ዕለትጦርነት ገጥመው፣ ኢትዮጵያውያኖቹ በማሸነፍ ላይ ሳሉ ንጉሠ ነገሥቱ፣ መጀመሪያ እጃቸው ላይ፤ ቀጥሎም ደረታቸውን በጥይት ስለተመቱ የኢትዮጵያው ሠራዊት ከሥፍራው በማፈግፈግ ሲለቅ ድሉ የ'ማህዲዎቹ' ኾነ። ንጉሠ ነገሥቱም ማታውኑ አረፉ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የሶቪዬት ሕብረት ባህር ዳር ላይ ፩ ሺህ ተማሪዎችን የሚያስተናገድ የቴክኒክ ትምህርት ቤት እንደምትሠራ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት አስታወቀ