ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/የካቲት 20
- ፲፯፻፸፪ ዓ/ም - በኢራን የተከሰተ የመሬት እንቅጥቅጥ ፪ መቶ ሺህ ሰዎችን አጠፋ።
- ፲፱፻፲፬ ዓ/ም - የብሪታኒያ ንጉዛት መንግሥት በራሱ ፈቃድ በግብጽ ላይ የነበረውን ሉዐላዊነት አቁሞ ነጻነትን ለግብጻውያን አሳልፎ ሲሰጥ የውጭ ጉዳይን፤ ግንኙነትን፤ የጦር ሠራዊትንና የግብጽ ሱዳንን አስተዳደር የሚመለከቱ ጉዳዮችን ግን በራሱ አስተዳደር ሥር አስቀረ።
- ፲፱፻፳፯ ዓ/ም - ለዱፖንት ኩባንያ ይሠራ የነበረው ዋላስ ካሮዘርስ ናይሎን (Nylon) ፈጠረ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የአብዮት ፍንዳታ፣ የወታደሩ አመጽ ተስፋፍቶ አዲስ አበባ የሚገኙ የ፬ተኛ ክፍለ ጦር፤ የጦር ሠራዊት፤ ዓየር ኃይል እና የዋና መሥሪያ ቤት ወታደሮች በከተማው ‘ቁልፍ’ ቦታዎችን በቁጥጥራቸው ሥር አዋሉ። ብዙዎችን የአክሊሉ ሀብተ-ወልድን ሚኒስቴሮች አስረው ያዙ። ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አቶ እንዳልካቸው መኮንንን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እና ጄኔራል አቢይ አበበን የመከላከያ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ። በወቅቱ አዲስ አበባ ላይ ሊካሄድ ተዘጋጅቶ የነበረው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ስብሰባ በረብሻው ምክንያት ተሰረዘ።
- ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - የመሬት እንቅጥቅጥ በአርሜኒያ እና አዘርባይጃን አገሮች ፩ ሺህ ፩ መቶ ሰዎች ሲገል፣ በሰሜን ኢራን ደግሞ ፫ ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል