ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ነሐሴ 16
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች በዛሬው ዕለት በየዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን የሚጀመረውን ጾመ ፍልሰታ የሚፈቱበት ቀን ነው።
- ፲፰፻፶፮ ዓ/ም - በጦርነት የተማረኩ ሰዎችን መብት ስለማስጠበቅና ስለማክበር የተዘጋጀው የጋራ ድንጋጌ (የጀኒቫ ኮንቬንሽን) በአሥራ ሁለት መሥራች አገሮች ተፈረመ። የቀይ መስቀል ማኅበርም አብሮ ተመሠረተ።
- ፲፰፻፺፮ ዓ/ም - በ፺፫ ዓመታቸው እስከሞቱ ድረስ ለ፳፯ ዓመታት ቻይናን የመሩት ዶንግ ዢያው ፒንግ ተወለዱ።