፲፱፻፫ ዓ/ም አንድ ሚሊዮንኛው የአዕምሯዊ ንብረት (patent) በዩናይትድ ስቴትስ የአዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ተመዘገበ። ይኼም የፍራንሲስ ሆልተን ውስጣዊ ቱቦ አልባ ጎማ ነው።

፲፱፻፷፮ ዓ/ም የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሪቻርድ ኒክሰን የ“ወተርጌት ቅሌት” (watergate scandal) ተብሎ በሚታወቀው ጉዳይ ምክንያት የፕሬዚደንት ስልጣናቸውን በማግሥቱ እንደሚለቁ ይፋ አደረጉ።

፲፱፻፹፪ ዓ/ም ኢራቅ ጎረቤቷን ኩዌትን በመውረር የኢራቅ አካል አደርገች። ይኼም ድርጊት የመጀመሪያውን የባህረ ሰላጤ ጦርነት የጫረው ድርጊት ነው