ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 26
- ፲፬፻፹፭ ዓ.ም. ክሪስቶፎሮ ኮሎምቦ የሂስፓኒዮላን ደሴት (የአሁኗ ሀይቲ ደሴትን እና የዶሚኒካን ሪፑብሊክን በመርገጥ የመጀመሪያው አውሮፓዊ ሆነ።
- ፲፱፻ ዓ.ም. - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት እና የታላቋ ብሪታኒያ መንግሥታት፤ ከዶሎ እስከ ሱዳንግዛት ድረስ ያለውን የኢትዮጵያን ድንበር ለማስመር ስምምነት ፈረሙ።
- ፲፰፻፳፬ ዓ.ም. የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆን ክዊንሲ አዳምስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (House of Representatives) በዓባልነት ተመርጠው መቀመጫቸውን ያዙ።
- ፳፻፩ ዓ.ም. በሩሲያ ውስጥ የአሜሪካ እና የሩሲያ ባለ ሙያዎች በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. ተቆፍሮ የተገኘውን የሰው አጽም የአገሪቱ የመጨረሻ ንጉሥ ዳግማዊ ዛር ኒኮላስ አጽም መሆኑን አረጋገጡ።