ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 15
- ፲፱፻፶፮ ዓ.ም. - ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲን ገድለሃል ተብሎ የተወነጀለው ሊ ሃርቪ ኦዝዋልድ፣ ዳላስ የፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞችና ቴሌቪዝን ድርጊቱን ለዓለም እየሰራጩ ሳሉ፤ ጃክ ሩቢ የሚባለው ሰው ኦዝዋልድን በሽጉጥ ገደለው።
- ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. - አምባገነኑ ጆሴፍ ዴዚሬ ሞቡቱ በኮንጎ የመሪነትን ሥልጣን በጉልበት ጨበጠ። በ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. የአገሪቱን ስም ቀይሮ ዛይር ተባለች። እሱም በአምባገነነንነት ሠላሣ ሁለት ዓመታት ከገዛ በኋላ በ፲፱፻፺ ዓ.ም. በኃይል ከሥልጣን ተወገደ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. - ዶናልድ ዮሃንሰን እና ቶም ግሬይ አፋር (ክልል) ክልል ውስጥ ከ ሦሥት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ዓመታት በፊት የኖረችውን የድንቅነሽን ዓጽም አገኙ።