ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 1
- ፲፰፻፷፬ ዓ.ም. - ለስድስት ዓመታት አፍሪቃ ውስጥ ጠፍቶ የነበረው የስኮትላንድ ተወላጅ ዶክተር ዴቪድ ሊቪንግስተን በታንጋኒካ ሐይቅ አካባቢ ኡጂጂ በሚባል ሥፍራ ላይ፣ በ ጋዜጠኛው ሄንሪ ሞርቶን ስታንሊ ተገኘ።
- ፲፱፻፲፪ ዓ.ም. በኮንጎ የካታንጋን ግዛት ነጥሎ ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. የዚያው ክልል ፕሬዚደንትነት የተመረጠውና የወቅቱ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ፓትሪስ ሉሙምባን ያስጠለፈና ያስገደለው ሞይስ ቾምቤ ተወለደ።
- ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. - የቀድሞው ኦቶማን ግዛት ከአከተመ በኋላ፣ አዲሷን የቱርክ ሪፑብሊክን የመሠረተው ሙስታፋ ካማል አታቱርክ አረፈ።