ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ታኅሣሥ 2
- ፲፱፻፲፩ ዓ/ም - የሩሲያው ተወላጅና የሥነ ጽሑፍ ሰው አሌክሳንደር ሶልዤኒትሲን በዛሬው ዕለት በኪስሎቮድስክ ተወለደ። ሶልዤኒትሲን በስታሊን ዘመን አድሀሪ በመባል ተወንጅሎ በሳይቤሪያ ግዛት ውስጥ በእሥራትና በግዞት በነበረበት ወቅት የጻፈው “የጉላግ አርቺፒላጎ” በተባለው ድርሰቱ በዓለም ታዋቂነትን ያተረፈ ጸሐፊ ነበር።
- ፲፱፻፴ ዓ/ም - የፋሺስት ኢጣልያ መንግሥት ኢትዮጵያ አገራችንን በግፍ ከወረረች በኋላ የተሰነዘረባትን ነቀፋ እና የንግድ እገዳ ምክንያት በማድረግ ከየዓለም መንግሥታት ማኅበር አባልነት ወጣች።
- ፲፱፻፴፱ ዓ/ም -የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ሕጻናት ዕርዳታ ድርጅት (UNICEF] ተመሠረተ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - ታዋቂው የአብዮት መሪ ቼ ጉቬራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጉባዔ ላይ ንግግር ሲያደርግ ያልታወቀ ሽብርተኛ ከውጭ በሕንጻው ላይ የሞርታር ጥይት ተኮሰ።
- ፲፱፻፸፬ ዓ/ም -የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት የፔሩውን ተወላጅ ሃቪዬር ፔሬዝ ደ ኩዌያርን የድርጅቱ አምስተኛ ዋና ጸሐፊ እንዲሆኑ መረጣቸው።