ታኅሣሥ ፲፫

  • ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የጃንሆይ አጎት ደጃች ወልደ ሥላሴ ለመንግሥት ሥራ ደሴ ደርሰው ሲመለሱ አደጋ ተፈጥሮ ቀበቶ ሳያስሩ ቆመው ሲፎክሩ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ራሳቸውን በኃይል ስለመታቸው ከተሳፋሪዎቹ መካከል እሳቸው ብቻ በአደጋው ሞቱ። ስለኾነም በአይሮፕላን አደጋ በመሞት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ እኒሁ የራስ መኮንን ወንድም ደጃች ወልደ ሥላሴ መሆናቸው ነው።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በሁለት የአስመራ ቡና ቤቶች ላይ በተወረወሩ ተወርዋሪ ፈንጂዎች በተከሰተው አደጋ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ በተያያዘ የኤርትራ ነፃነት ግንባር አሰብ ወደብ አካባቢ የሰነዘረው ጥቃት ሦስት የጭነት መኪናዎችን አውድሟል።
  • ፲፱፻፺፭ ዓ/ም - በ፲፱፻፳፪ ዓ/ም የተደነገገውን ‘የኢትዮጵያ ዜግነት’ ሕግ በመሻር የሚተካው፤ ስለኢትዮጵያ ዜግነት የወጣው አዋጅ ቁጥር ፫፻፸፰/፲፱፻፺፮ ከዚህ ዕለት ጀምሮ ሕግ ሆኖ እንደሚጸና በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታወጀ።