ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሚያዝያ 4
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም ለአሥራ ሁለት ዓመታት አገራቸውን በፕሬዚደንትነት የመሩት አሜሪካዊው ፍራንክሊን ዴላኖ ሩዝቬልት በዛሬው ዕለት አለፉ። ሩዝቬልት የአሜሪካ ፴፪ኛው ፕሬዚደንት ነበሩ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የሶቪዬት ሕብረት የመጀመሪያውን ጠፈርተኛ፣ የ፳፯ ዓመት የአየር ኃይል አባል ዩሪ ጋጋሪንን በመኖራኩር ተኮሰች። ጋጋሪን በጠፈር በረራ ምድርን ለአንድ ሰዓት ከአርባ ደቂቃ ያህል ከዞረ በኋላ ወደመሬት ተመልሷል።