ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መጋቢት 30
- ፲፱፻፴፰ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመጀሜሪያ ጊዜ የዓለም አቀፍ በረራውን ከአዲስ አበባ ተነሥቶ በአስመራ በኩል በምስር ርዕሰ ከተማ ካይሮ ላይ አከናወነ።
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - በኬንያ ‘የአፍሪቃ ኅብረት እንቅስቃሴ’ መሪ የነበሩት ጆሞ ኬንያታ ድርጅቱ በቅኝ ገዝዎቻቸው ላይ የ’ማው ማው’ ሽብርን አካሂዷል በሚል በተሰነዘርበት ክስ ኃላፊነት አለብዎ ተብለው ለሰባት ዓመት የጽኑ እሥራት ቅጣት ተፈረደባቸው።
- ፲፱፻፺፯ ዓ/ም - የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ አቡነ ዳግማዊ ዮሐንስ-ጳውሎስ የቀብር ሥነ ሥርዓት በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ ‘ባዚሊካ’ የዓለም መሪዎችና ምዕመናን በተገኙበት ተከናወነ።