ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መጋቢት 1
- ፲፭፻፺፱ ዓ/ም - በጎጃም ምድር ጎል በተባለ ሥፍራ የንጉሥ አጼ ያዕቆብ እና የአጼ ሱስንዮስ ሠራዊት ጦርነት ገጥመው ድሉ የሱስንዮስ ሆነ። አጼ ያዕቆብ እና ጳጳሱ ዳግማዊ ጴጥሮስ በዚሁ ጦርነት ላይ ሞቱ።
- ፲፰፻፹፩ ዓ/ም - ዮሐንስ ፬ኛ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በትልቅ ጦርነት ከደርቡሾች ጋር ሲዋጉ መተማ ላይ በእነሱ ውጅ ወደቁ። ሱዳኖቹ አንገታቸውን ቆርጠው እንጨት ላይ ሰክተው ገበያ ለገበያ ለሕዝባቸው አሳዩት።
- ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - የአልቃይዳ መሥራችና መሪ ኦሳማ ቢን ላደን በዚኡ ዕለት ተወለደ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ከኢትዮጵያ የሠራተኞች ማኅበራት ድርጅት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቁ።