- ፲፭፻፴፫ ዓ/ም - ኢትዮጵያን የወረረውን ግራኝ መሐመድን ለመከላከል የዘመተውን የ|ብርቱጋል ሠራዊት የመራው ኤስቴቫዎ ዳጋማ ወንድሙን ክሪስቶቫዎ ዳጋማ ን ከአራት መቶ ወታደሮችና መቶ ሃምሳ ባሪያዎች ጋር ትቶ ከምጽዋ ወደብ ወደአገሩ ተጓዘ።
- ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የቀድሞው የሞሮኮ ንጉሥዳግማዊ ሀሳን (በአረብኛ: الحسن الثاني)፤ (ዕ.ሞ ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓ/ም) በዚህ ዕለት ተወለዱ። ንጉሡ የዛሬው የንጉሥ ሞሀመድ ራብአዊ (በአረብኛ: محمد السادس) አባት ናቸው።
- ፲፱፻፴፬ ዓ/ም - ሪቻርድ ራውንድትሪ (Richard Roundtree). ሪቻርድ በዋና ተዋናይነት <<ጆን ሻፍት>> (John Shaft) ሆኖ <<ሻፍት ኢን አፍሪካ>> (Shaft in Africa) በተባለው ፊልም ላይ ከ'ጭራ ቀረሽ'ዘነበች ታደሰ እና ደበበ እሸቱ (ዋሳ Wassa) ጋር ሠርቷል፤ በዛሬው ዕለት ተወለደ።
- ፲፱፻፴፱ ዓ/ም - የእንግሊዝ ልዕልት፣ (አሁን ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ) እና የሌፍተናንት (አሁን የኤዲንበራ መስፍን ልዑል) ፊሊፕ የጋብቻ እጭት ይፋ ተደረገ።