ውክፔዲያ:ቀላል መማርያ/ገጽ 3
ሌላውን ጽሑፍ ስለ ማያያዝ:
- መያያዣ ለሌሎች መጣጥፎች በቀላል ሊፈጥሩ ይቻላል። ለምሳሌ በመጣጥፍዎ ውስጥ «ግሥላ» የሚልን አንድን ቃል ቢኖር ስለ ግሥላዎች ወደሆነው ጽሁፍ ለማያያዝ፣ ዝም ብለው ሁለት ባለ-ማእዘን ቅንፍ ([[ ]]) ይጨመራሉ። ስለዚህ [[ግሥላ]] በመጻፍ መያያዣውም እንዲህ ግሥላ ይመስል ነበር።
- ከዚህ በላይ በመያያዣው ውስጥ የሚታዩትን ቃላት ለመቀየር ይቻላል። እንዲህ ለማድረግ የፒፓ ምልክት ( | ) ከመያያዣው አርዕስት ቀጥሎ ጨምረው ለመታየት የሚፈልጉትን ይጻፉ።
- እንግዲህ [[ግሥላ|ስለ ግሥላዎች የሆነው መጣጥፍ]] በመጻፍ እንዲህ ይመስል ነበር፦ ስለ ግሥላዎች የሆነው መጣጥፍ።
- የውጭ ድረ ገጾችን ማያያዝ ደግሞ ይቻላል። ለምሳሌ [http://www.google.com ጉግል] (ያለ ፒፓ ምልክት) እንዲህ ይታያል፦ ጉግል