ኰሙኒስም
ኰሙኒስም በፖለቲካ ወይም [[ኅብረተሠብ ጥናት ማለት የምረታ ባለቤትነት ሁሉ የጋራ እንዲሆን የሚጥረው ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም፣ ፍልስፍናና እንቅስቃሴ ነው። ቃሉ ከሮማይስጥ /ኮሙኒስ/ «የጋራ» ደርሷል።
በአለማችን የታወቀው ኰሙኒስም ማርክሲስም-ሌኒኒስም ሲሆን የኰሙኒስት ርዕዮተ-አለም ካሉት አምስቱ መንግሥታት አራቱ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ናቸው። እነርሱም ቬትናም፣ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ፣ ኩባ፣ እና ላዎስ ናቸው። አምስተኛው ወይም ስሜን ኮርያ «ጁቼ ኰሙኒስም» የተባለው ርዮተ አለም ሲኖረው ከ1937 እስከ 1983 ዓም ድረስ እርሱ ደግሞ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ይባል ነበር፤ እንዲሁም በርካታ ሌሎች አገራት ከ1983 አስቀድሞ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ሆነው ነበር። ሆኖም ብዙ ጊዜ የማርክስ መርሆች በተግባር ወደ እውነትኛ ኰሙኒስም ወይም ለሕዝቡ ጸጥታና ደኅንነት ሳይሆን ወደ ግፍና አምባገንነት ይመሩ ነበር።