ኮካ-ኮላ (ወይም ኮካ) በአለም ዙሪያ የሚሸጥ ለሥላሣ መጠጥ ነው።

ኮካ-ኮላ
ሞንትሬያል, ካናዳ.

ኮካ-ኮላ መጀመርያ የተፈጠረ በ1878 ዓ.ም. በአትላንታ አሜሪካ በዶ/ር ጆን ፔምበርቶን ነበረ። መጀመርያ ሀሣቡ ማነቃቂያ መድኃኒት እንዲሆን ነበር። ኮካ-ኮላ የሚለው ስም የተወሰደበት ምክንያት በመጀመርያ የኮካ ቅጠልና የኮላ ፍሬ በውስጡ ስለነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ግን እነዚህ አትክልት አይገኙበትም።

1886 ዓ.ም. ጀምሮ በብርሌ ይሸጥ ጀመር። በ1947 ዓ.ም. ደግሞ በቆርቆሮ ይሸጥ ጀመር።

ዛሬ የኮካ-ኮላ ድርጅት ብዙ ሌሎች አይነት ለሥላሣዎች ይሠራል። በአለም ዙሪያ በ1 ሴኮንድ ውስጥ፣ ከኮካ-ኮላ ድርጅት የወጡ የ10,450 ለሥላሣዎች እየተጠጡ ነው።