ክሮኤሽያ
(ከክሮሽያ የተዛወረ)
ክሮኤሽያ ወይም ክሮሽያ (ክሮሽኛ፦ Hrvatska /ሕርዋትስካ/) የአውሮፓ አገር ነው። የቀድሞ ዩጎስላቪያ ክፍላገር ነበረ።
Republika Hrvatska |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: "Lijepa naša domovino" |
||||||
ዋና ከተማ | ዛግሬብ | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ክሮኤሽኛ | |||||
መንግሥት {{{ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር |
ኮልንዳ ግራባር-ኪታሮቭች አንድረይ ፕሌንኮቪች |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
56,542 (126ኛ) 1.09 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት |
4,190,700 (115ኛ) |
|||||
ገንዘብ | ዩሮ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +1 | |||||
የስልክ መግቢያ | +385 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .hr |
«ክሮኤሽያ» በእንግሊዝኛ የ«Croatia» ኣጠራር ያንጸባርቃል።[1] ይህም አጻጻፍ ከሮማይስጥ /ክሮዋቲያ/ ሲሆን ከኗሪ ስም /ሕርዋትስካ/፣ ሕዝቡም /ሕርዋቲ/፣ ቋንቋውም /ሕርዋትስኪ/ ደረሰ። የስላቪክ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሆኑት ክሮአት ሕዝብ በዙሪያው ከ810 ዓም ገደማ ታውቀዋል፣ ከ600 ዓም አስቀድሞ ተዘዋዋሪዎች እንደ ነበሩ ይታመናል፤ ከእስኩቴስ ወይም ከሳርማትያ እንደ ደረሱ በብዙ መምህሮች ይታመናል። ትርጉሙ ተከራካሪ ሆኗል፤ በአንዳንድ አስተሳሰቦች ግን ከጥንታዊው ሀገር «አራኾሲያ» (በአሁኑ አፍጋኒስታን፣ ጥንታዊ ፋርስኛ /ሓራሑዋቲስ/) ጋር ዝምድና ይኖረዋል።
- ^ እንግሊዝኛው አጠራር የታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ ምሳሌ ነው።