ከንቲባ ገብሩ (1845 - 1949) እውነተኛ ስማቸው ጎባው ደስታ ሲሆን የአቶ ደስታ ወልደ እስይ እና ወይዘሮ ትርንጎ ተክሌ ልጅ ነበሩ። የተወለዱትም ጎንደር ውስጥ አለፋ ጣቁሳ የሚባል ቦታ ሲሆን፣ ወላጆቻቸው መሳፍንቶች ስላልነበሩ ብዙ እንግልት ደርሶባቸው ካደጉ በሁዋላ በሚስዮን ወደ ውጭ ሄደው ተምረው ሲመለሱ ባሳዩት ችሎታ በራስ መኮንንሐረር ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ። ቀጥሎም ከአድዋ ጦርነት በሁዋላ በዓፄ ምኒልክ የመጀመሪያው የጎንደር ከተማ ከንቲባ ሆኑ። በዓፄ ዮሐንስ ዘመን በተካሄደው ጦርነት በሱዳኑ መሪ የታሰሩትን እስረኞች እንዲያስለቅቁ ተልከው የተደራደሩት እሳቸው ነበሩ። የእስረኞቹ መለቀቅ ያናደዳቸው እንግሊዞች ግን ሴራ ፈጥረው ዓፄ ምኒልክ እንዲይስርዋቸው አድርገዋል። ከእስር የተለቀቁትም ንግስት ቭክቶሪያ ስትሞት ነበር። በ1930 የመጀመሪያ ፓርላማ ምክትል ፕሬዘደንት ሆኑ። ጣሊያኖች ከኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያ ፓርላማ ፕሬዘደንት ሆኑ።

ከንቲባ ገብሩ ከሴት ልጃቸው ጋር 1906 በፋሲል ግምብ

ገብሩ አማርኛኦሮምኛጀርመንኛፈረንሳይኛእንግሊዝኛ ይናገሩ ነበር። [1]


ማጣቀሻወች ለማስተካከል

  1. ^ http://www.dacb.org/stories/ethiopia/gebru_desta.html"Stars Archived ጁላይ 2, 2015 at the Wayback Machine that glitter