ኦርጦፖሊስ (ግሪክ፦ Ὀρθόπολις) በሲክዮን ነገሥታት ዝርዝር የአፒያ (በኋላ ሲክዮን) ንጉሥ ነበር።

ካስቶርን የጠቀሱት ጸሐፊዎች ኦርጦፖሊስ 63 ዓመት እንደ ነገሠ ይላሉ።[1][2] ከአባቱ ፕሌምናዮስ በኋላ እና ከተከታዩ ማራጦኒዮስ በፊት ገዛ።

ጸሐፊው ፓውሳኒዩስ በተረከው ትውፊት፣ የፕሌምናዮስ ሕጻን ልጆች ሁሉ እንዳለቀሱ ወዲያው ሞቱ። በመጨረሻ ግን ዴሜተር (አረመኔ ሴት ጣኦት) ማረችው፣ ልጁን ኦርጦፖሊስ አሳደገችና በሕይወት ኖረ።[3] በፓውሳኒዩስ ጽሑፍ ከኦርጦፖሊስ ቀጥሎ ያለው ቅድም-ተከተል ከሌሎች ምንጮች ይለያያል። እሱ እንደ ጻፈው ማራጦኒዮስ የኦርጦፖሊስ ተከታይ አይባልም፤ ይልቁንም የኦርጦፖሊስ ሴት ልጅ ቅሪውሶርጤ፣ የቅሪውሲርጤም ወንድ ልጅ (በአፖሎ) ኮሮኖስ ይጠቀሳሉ። ይህም ኮሮኖስ በኋላ የነገሡትን ፪ ወንድ ልጆች ኮራክስ እና ላሜዶን እንደ ወለዳቸው ይለናል።

ቀዳሚው
ፕሌምናዮስ
አፒያ ንጉሥ ተከታይ
ማራጦኒዮስ
  1. ^ የአውሳብዮስ ዜና መዋዕል
  2. ^ የጀሮም ዜና መዋዕል
  3. ^ "Classical E-Text: PAUSANIAS, DESCRIPTION OF GREECE 2.1 - 14". theoi.com (2011). በ5 February 2014 የተወሰደ.