እንኮይ
እንኮይ (Ximenia americana L.) በኢትዮጵያ የሚበቅል እጅግ ጣፋጭ የሆነ ቢጫ ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ ነው።
የእንኮይ ተጨማሪ ጥቅም
ለማስተካከልፍራፍሬውን በብዛት መብላት ትልን ይገድላል።
የእንኮይ ዘር ግን መርዛም ነው።[1]
በአንድ ናይጄሪያ ዩኒቨርሲቲ ምርመራ፣ የተለያዩ ተውሳኮችን እንደሚገድል ተረጋገጠ።[2] የፍሎሪዳ ክፍላገር አሜሪካ ጥንታዊ ኗሪዎች ልጡ በጡንቻ ወይም ድድ ሕመም ላይ ማከሙን ያውቁ ነበር።[3]
ቅጠሉ ትንሽ መርዝ አለውና ሳይበላ በደንብ መበሰል ያስፈልጋል። ቅጠሉ ጉሮሮ ሲደርቅ፣ ለአሜባ፣ ለውሻ በሽታ ያገለግላል።
እንኮይ ተስማሚ የሆነ አየር ጠባይና መሬት
ለማስተካከልከ2000 ሜትር በታች እስከ 7 m. ይደርሳል። በቆላና በገሞጂ አገራት ይገኛል።
የእንኮይ አስተዳደግና እንክብካቤ
ለማስተካከልቅጠለ ረገፍ ዛፍ ወይም ቊጥቋጥ ነው። ቅጠሉ እንደ ለውዝ (አልመንድ) ይሸታል።
- ^ አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
- ^ Short Communication: Studies of antimicrobial activity and chemical constituents of Ximenia americana. DS Ogunleye and SF Ibitoye, Trop J Pharm Res, December 2003, 2(2), pages 239-241 (abstract)
- ^ 50 Common Native Plants Important In Florida's Ethnobotanical History by Ginger M. Allen, Michael D. Bond, and Martin B. Main. University of Florida IFAS Extension. https://web.archive.org/web/20120426161709/http://edis.ifas.ufl.edu/uw152