?አልመንድ

ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: አትክልት (Plantae)
ክፍለመደብ: Rosales
አስተኔ: Rosaceae
ወገን: የኮክ ወገን Prunus
ዝርያ: አልመንድ P. dulcis

አልመንድ (Prunus dulcis) የለውዝ አይነት የሚሰጥ ዛፍ አይነት ነው። እንዲያውም ዛፉ በኮክ ወገን ይመደባል፤ ለውዙም (ወይም 'አልመንድ') የተክሉ ዘር ነው።

«ለውዝ» ብዙ ጊዜ ኦቾሎኒ ማለት ሲሆን፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን ውስጥ «ለውዝ» ሲጠቀስ አልመንድ ነው።

አልመንድ ደግሞ ለደምና ለጉበት ጤንነት መልካም በመሆን በትንሹ ኮሌስትሮልን ዝቅ እንደሚያደርግ ታውቋል።[1]

  1. ^ ናፍቆት መጽሔት ቁ. 64, May/June 2014 እ.ኤ.አ. ገጽ 25