ኤቂውረውስ (ግሪክ፦ Ἐχυρεύς) በሲክዮን ነገሥታት ዝርዝር የአፒያ (በኋላ ሲክዮን) ንጉሥ ነበር።

ካስቶርን የጠቀሱት ጸሐፊዎች ኤቂውረውስ 55 ዓመት እንደ ነገሠ ይላሉ።[1][2]ማራጦስ በኋላ እና ከተከታዩ ኮራክስ በፊት ገዛ።

ፓውሳኒዩስ ጽሑፍ ግን ከኦርጦፖሊስ ቀጥሎ ያለው ቅድም-ተከተል ከሌሎች ምንጮች ይለያያል፤ በማራጦኒዮስ፣ ማራጦስና ኤቂውረውስ ፋንታ አንድ ንጉሥ ኮሮኖስ ብቻ ይጠቀሳል።

በጀሮም ዜና መዋዕል ዘንድ፣ በዚሁ ዘመን ዳናውስግብጽ ወጥቶ ስጠነላዎስን ከአርጎስ አባረረውና አርጎስን ገዛ።

ቀዳሚው
ማራጦስ
አፒያ ንጉሥ ተከታይ
ኮራክስ
  1. ^ የአውሳብዮስ ዜና መዋዕል
  2. ^ የጀሮም ዜና መዋዕል