አምበሾክ
(ከኣምበሾክ የተዛወረ)
አምበሾክ (ሮማይስጥ፦ Annona muricata) ከሜክሲኮ እስከ ስሜናዊ ደቡብ አሜሪካ ድረስ የሚገኝ ሁሌ ለምለም ቅጠለ ስፋፊ አባባማ ዛፍ አይነት ነው። ከዚህ ደግሞ ዛሬ በፊልፒንስና በደቡብ-ምሥራቅ እስያ ይበቅላል። ኢትዮጵያም ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው። በጣም በሞቀ አገር ስለሚበቅል ከ3 ሴንቲ ግሬድ በታች ሊኖር አይችልም።
ፍሬውን መብላት ከባድ ሆኖ አብዛኛው ጊዜ ለጭማቂ ይጠቅማል። ብዙ ካርቦሃይድሬት በተለይም ፍሩክቶስ አለበት። ደግሞ ቪታሚን-ሲ፣ ቪታሚን-ቢ1፣ ቪታሚን-ቢ2፣ ይበዛሉ። ፍሬው፣ ዘሩ፣ እና ቅጠሉ በተገኝባቸው አገሮች እንደ ተፈጥሮአዊ መድኅኒት ይጠቅማል። ከዚህ በላይ በአንዳንድ ትንተና ዘንድ የዛፉ ቅጠልና ግንድ የነቀርሳ (ካንሰር) ህዋስ እንደሚያጥፋ ችሎታ አለው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |