ኢግሪሽ-ሐላብ ወይም ኢግሪሽ-ሐላም ከ2127-2115 ዓክልበ. ግድም የኤብላ ንጉሥ ነበር። የኤብላ ጽላቶች የተባሉት ሰነዶች ክምችት ከርሱ ዘመን ጀምሮ ይታወቃል። የኤብላ ግዛት ያንጊዜ በሶርያ አካባቢ ሰፊ ነበር። የማሪ ንጉሥ ኢብሉል-ኢል ግን በተወዳዳሪው በኤብላ ላይ ጦርነት እየሠራ ከኤብላ አንዳንድ መንደሮች ያዘ።

የኢግሪሽ-ሐላብ ንግሥት «ከስዱት» ስትሆን ልጃቸው ኢርካብ-ዳሙ ወደ ዙፋኑ ተከተለው። ሴት ልጃቸው ሳኒብ-ዱሉም ተባለች።

ቀዳሚው
አዱብ-ዳሙ
ኤብላ ንጉሥ
2127-2115 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኢርካብ-ዳሙ