ኢቢኤስ
ኢቢኤስ (ኢ.ቢ.ኤስ.፣ EBS፤ Ethiopian Broadcasting Service ወይም EBSTV) በስልቨር ስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ በአሜሪካ አገር በ2000 ዓም የተመሠረተ የሜዲያ ድርጅት ነው። የሚያዝናኑ ቴሌቪዥን ትርዒቶች ለኢትዮጵያውያን በአለም ዙሪያ በዲያስፖራም ሆነ በአገርቤት ያቀርባል።
እስቱዲዮዎች (የመሣያ ክፍል) በሜሪላንድና በአዲስ አበባም አሏቸው። ተወዳጅነትና ዝና ካገኙት አማርኛ ትርዒቶቻቸው መካከል፦
- ቴክ ቶክ ዊስ ሰሎሞን - «የመረጃ ኅብረተሠብ» በተያዘ (አስተናጋጅ፦ ሰሎሞን ካሣ)
- ኢትዮጵያን እንወቅ - ግሩም ሥፍራዎች ሀገር ቤት (ዮዲት ሽፈራው)
- የቤተሠብ ጨዋታ - እንደ ድሮው አሜሪካዊ ጨዋታ-ትርዒት «ፋሚሊ ፊውድ»፣ በአማርኛ (እሸቱ መለሰ)
- እንቆቅልሽ - ስለ ባሕል ወግ የጠያየቀ ጨዋታ-ትርዒት (አበበ ፈለቀ)
- ትዝታችን - በኢትዮጵያ ያለፈውን ክፍለ ዘመን ትዝታና ታሪክ ያቀርባል (ዮናስ ከበደ)
- ሰይፉ በኢቢኤስ - የውይይት ትርዒት (ሰይፉ ፋንታሁን)
ብዙ ሌሎችም የዜና፣ ድራማ፣ እስፖርት፣ ሙዚቃ፣ አበሳሰል፣ ማዝናናት ትርዒቶች ይገኙበታል።
የውጭ ማያያዣ
ለማስተካከል- የኢቢኤስ ዋና ድረ ገጽ Archived ኦገስት 6, 2017 at the Wayback Machine