አጋ
አጋ (ወይም አካ) በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ በሱመር የኪሽ ከተማ ንጉሥ ነበረ።
አጋ በጊልጋመሽ ትውፊት ደግሞ ይጠቀሳል፤ የጊልጋመሽ ከተማ ኡሩክን እንደ ከበበ፣ ጊልጋመሽም እንዳሸነፈው ይላል።[1]ከሦስተኛም ምንጭ የቱማል ጽሑፍ[2]፣ ጊልጋመሽ ኒፑርን ከአጋ እንደ ያዘ መገመት ይቻላል።
የሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር፣ የጊልጋመሽ ትውፊት እና የቱማል ጽሑፍ ሁላቸው አጋ የኤንመባራገሲ ልጅና ተከታይ እንደ ነበር በማለት ይስማማሉ። ይህ ኤንመባራገሲ የኪሽ ንጉሥ ሲሆን ከሥነ ቅርስ በእውኑ እንደ ነገሠ ታውቋል። ስለዚህ አጋ እና ጊልጋመሽ እራሳቸው ታሪካዊ ነገሥታት እንደ ነበሩ ይታስባል። በአጭር አቆጣጠር ምናልባት 2370 ዓክልበ. ግድም ነገሠ። የሱመር ነገሥታት ዝርዝር ግን ለመጀመርያው ዘመን ብዙ ጊዜ የማይመስል ቁጥር አቅርቦ እንደ ሆነ፣ አጋ በኪሽ ለ625 ዓመታት እንደ ነገሠ ይላል።
ምንጮች
ለማስተካከል- ^ George, Andrew (1999). The epic of Gilgamesh: the Babylonian epic poem and other texts in Akkadian and Sumerian. London: Allen Lane Penguin Press. ISBN 978-0-7139-9196-3.
- ^ "ETCSLtranslation : t.2.1.3; The history of the Tummal". Archived from the original on 2018-09-24. በ2008-04-22 የተወሰደ.
የውጭ መያያዣ
ለማስተካከል- ETCSL - Text and translation of Gilgamesh and Aga Archived ሜይ 2, 2019 at the Wayback Machine (alternate site Archived ሜይ 5, 2008 at the Wayback Machine)