አጊሲውምባ (ሮማይስጥ፦ Agisymba) በሮማዊው ታሪክ ጸሐፊ ቶለሚ ዘንድ በ1ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. በዛሬው ደቡብ ቻድ አካባቢ የተገኘ ጥንታዊ አገር ነበር።

አጊሲውምባ በዛሬው ደቡብ ቻድ በቻድ ሐይቅ ጎን ተገኘ።

ቶለሚ (150 ዓም ግድም) እንደ ጻፈ፣ በ42 ዓም ሮማዊው አለቃ ፍላኩስ ሴፕቲሚዩስ እስከ ቻድ ሐይቅና ከዚያ ማዶ ደረሰ፣ አገሩም አጊሲውምባ ተባለ። አውራሪስጉማሬ በሐይቁ ዙሪያ የሞላበት አገር እንደ ነበረ ገለጸ። ከዚያ በ82 ዓም ሌላ ሮማዊ ተጓዥ ጁሊዩስ ማቴርኑስ በሁለተኛው ጉዞ እስከ አጊሲውምባ ድረስ ሄዶ አንድ አውራሪስ ይዞ እንደ ተመለሰ ተጽፏል። ከ75 እስከ 84 ዓም ድረስ የአጊሲውምባ ሕዝብ ለጋራማንቴስ ንጉሥ ተገዥ እንደ ነበር ጨመረ፤ ጋራማንቴስም በአሁኑ ደቡብ ሊብያ የተገኘ ብሔር ነበር።