አንድህዋሴ
አንድህዋሴ ዘአካላት የተለያዩ ሥራዎችን እንደ መመገብ፣እንቅስቃሴ ማድረግ፣ፅድጃ፣ ተዋልዶ፣ሥርዓተ ልመት እና የመሳሰሉትን በአንድ ሕዋስ ብቻ ያከናውናሉ፡፡ አንድህዋሴ ዘአካላት፡- ለምሳሌ አሜባ፣ ፖራሚስዬም፣ ባክቴሪያ እና እርሾ መዘርዘር ይቻላል፡፡እነዚህ ዘአካላት አብዛኛዎቹ በውሃማ ምቹጌ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ከሐይቅ፣ ከወንዝ፣ ከጉድጓድ ውሃ እና ከሌሎችም ውስጥ የባለአንድ ሕዋስ ዘአካላት ናሙና በመውሰድ በማይክሮስኮፕ መመልከትይቻላል፡፡
አንድህዋሴ ዘአካላት በአወቃቀር፣ በመጠን፣ በሕዋስ አወቃቀር እና ሥራዎች ልዩነት አላቸው፡፡ ከባለአንድ ሕዋስ ዘአካላት ውስጥ አሜባና ፓራሚሲየም እንስሳትን የሚመስል እንቅስቃሴ ያሳያሉ፡፡ ከባለ አንድ ሕዋስ ዘአካላት ውስጥ እንደ ክሎሬላ ያሉት በብርሃን አስተፃምር ምግባቸውን ያዘጋጃሉ፡፡ ኢዮግሊና፣ አሜባና ፓራሚስዬም በፕሮቲስታ ሥፍን ሥር ይመደባሉ፡፡ እንደ ኢዮግሊና ያሉት ደግሞ የእንስሳትና ዕፅዋት ባህሪ ያሳያሉ። ከእንስሳት ጋር የሚያመሳስለው አመጋገቡ እና እንቅስቃሴው ሲሆን፤ የፀሐይ ብርሃን ሲያገኝ እንደ አረንጓዴ እፅዋት ምግቡን ማዘጋጀት መቻሉ ከእፅዋት ጋር ያመሳስለዋል፡፡[1]
- ^ የስምንተኛ ክፍል ባዮሎጂ የተማሪ መጽሐፍ