ራያ ማለት በስሜን ወሎ እና በደቡብ ትግራይ ሰፍሮ የሚገኝ ነው። ይህ ህዝብ የራሱ የሆነ ባህል እና ወግ፡ ማለትም እንደ አነጋገር፡ አለባበስ፡ የሰርግ ፡ የለቅሶ ስነስራአት ያለው ኩሩ እና ጀግና ህዝብ ነው። የራያ በመቻቻል በህብረት በአንድ ላይ ተከባበሮ የሚኖር ህዝብ ሲሆን የአለባበስ ባህሉ ሌላው የሚደነቅለት አና ባህላዊ ጭፈራው ሲያዩት የሚያስግርም አና የሚያስድስት ነው። ከባህላዊ ጭፈራዎቹ እንደ "ጉማየ" "መጋልዋ" ፡ ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ህዝቡ የሚኖርበት አከባቢ እንደሚከተለው ይዋሰናል። በሰሜን እንደርታ፡ በደቡብ የጁ፡ በምስራቅ አፋር እንድሁም በምእራብ ላስታ ያዋሱኑታል። የከተሞች ስም ለመጥቀስ ያክል አላማጣ፡ ቆቦ፡ ኮረም፡ ማይጨው፡ መሆኒ ፣ጨርጨር፣ባላ፣ባንድራ፣ጋርጃለ፣ትዖ፣ኩኩፍቶ፣ህጅራ፣ሃደ ኣልጋ፣ጥሙጋ፣ዋጃ ፣መርዋ፣ሽኮማጆ፣ሃሸንገ።በ2013ዓም ራያ ጨርጨር ወደ ነበረችበት ወረዳነቷ ተመልሳለች።

ነገር ግን የራያ ባላ ማ/ሰብ ከጨርጨር ስነልቦና ስለሚለየ ጉርብትና እንጅ የአላማ አንድነት ስለላቸዉ ማህበረሰቡ ራያ ባላ ወረዳ ራሱን ችሎ ተቋቋመ።

Yasin al[1]i spa raya[Spartacus Raya book of Rayanizim 1]



በራያ ላይ ማነው የሚመለከተው?

############################


ከኤቦ ተራራ እስከ አላ ወንዙ ድረስ የሰፈሩ ተመሳሳይ ባህል፣ስነልቦና፣ማንነት፣ታሪክ ያላቸው ማህበረሰቦች ራያ ይባላል።በውስጡ ከ15 የማያንሱ ወረዳዎች የያዘ በሁለት ክልሎች መካከል የሚገኝ ቀደምት ህዝብ ራያ በመባል ይጠራል።

➡️ራያ ከአካባቢያቸው አልፈው ለሀገር ብዙ ነገር ማበርከት የሚችሉ እና ሀገር መምራት የሚችሉ በርካታ ልጆች አሏት።ይሁን እንጂ የወቅቱ ፖለቲካ በፈጠረው ልዩነት ሁሉም የራያ ተወላጆች በተለያዩ ጎራዎች ተሰልፈው የራያን ህዝብ ችግር እንደመፍታት የችግሩ ምንጭ መሆን ከጀመሩ ሰነባብተዋል።

➡️የራያ ህዝብ ማንነቱን ለማስከበር ለዘመናት ጥያቄ እየጠየቀ ቢመጣም ፤ህጋዊ በሆነ መንገድ ህጋዊ የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ መስርቶ መንቀሳቀስ ከጀመረ 3 ዓመት አድርጓል።ከጅምሩ ኮሚቴው ይዞት የተነሳው ሀሳብ 3ቱ የራያ ወረዳዎች ማለትም ራያ አዘቦ፣ራያ ኦፍላ፣ራያ አላማጣ ወደ ወሎ የመመለስ አላማ አንግቦ ሲሆን በዚያን ሰዓት ሁሉም አንድ ሁኖ ትግሉን ከሚደግፉ አካላት ጋር እየተጋገዘ አንድነቱን አጠንክሮ እየተጓዘ ነበረ።መሃል ላይ በግለሰቦች የስልጣን ሽኩቻ(በዶ/ር ሲሳይ እና በአገዘው ሕዳሩ)አለመስማማት ሁለት ጎራ ከፍለው የአላማ እና የትግል ልዩነት ፈጥረው ህዝቡ አንድ ሁኖ ቀንደኛ ጠላቱ የሆነውን ወያኔ እንዳይታገል በየአቅጣጫው ጥላቻ እየሰበኩ ለዘመናት አንድ ሁኖ ተለያይቶ የማያውቀውን ህዝባችን በታትነው የጠላት መጫወቻ አደረጉት።በነዚህ ኤሊቶች ምክንያት ምንም የማያውቀው ወጣት በስም ትግል በየግዜው በተለያየ ቦታ እየወደቀ ይገኛል።

➡️ከሁሉም የሚከፋው ደግሞ ህዝቡ በጨካኙ ወያኔ ቀዬውን ለቆ ለረሀብ እና ለመከራ ተጋልጦ እያዩ ልዩነታቸው ትተው አንድ ሁነው የህዝባቸው ችግር እንዳይፈቱ ለማይረባ ፖለቲካ ብለው በወንድማሞች ህዝቦች መካከል የማይፋቅ ጥላቻ ለመፍጠር ዕንቅልፍ አጥተው ማደራቸው ነው።የተፈናቀለው ህዝብ የነሱ እንዳልሆነ፣መሄጃ አጥቶ በረሀብ እየተሰቃየ ያለው ህዝብ የነሱ እንዳልሆነ ጆሮ ዳባ ብለው የፖለቲካ ስራ መስራታቸው ስታይ ደግሞ በጣም ያማል።

➡️አንዱ እኔ ብቻ ነኝ ራያ ሌላው አይመለከተውም ይላል።

➡️ሌላው ደግሞ አይ ለኔ ነው የሚቀርበው እኔ ነኝ ወኪሉ ይላል።

➡️ሌላው ደግሞ ከማንም ሳይሆን በዝምታ በእሱ ዕጣፈንታ እንደሚጨቃጨቁ እያወቀ በዝምታ የሚመለከት ታያለህ።

👉👉👉ሰፊው ህዝብ የሁሉንም ጭሆት እያየ ነፃነትን በሩቅ እየናፈቀ ከችግሩ ጋር ዉሎ ያድራል።የሚጨንቀው ደግሞ ለቀጣይም የተሻለ ተስፋ አለማየቱ ነው።

➠በራያ ያሉ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የማንነት አስመላሽ ኮሚቴዎች እንዲሁም የበጎአድራጎት ማህበር ሁሉም በራያ ጉዳይ ይመለከታቸዋል።በመሆኑም ሁሉም እንትና ነው የሚመለከተው ሳይል በጋራ ልዩነታቸው ይዘው ተከባብረው አንድ በሚያረጋቸው ጉዳይ አንድ እየሆኑ ለህዝባቸው መድረስ አለባቸው።

➠በራያ ጉዳይ  አብኑ፣ራዴፓው፣አማራ ብልፅግናው፣ትግራይ ብልፅግናው ሁሉም ይመለከተዋል።ሁሉም የራሱን ሀሳብ ለገበያ ያቅርብ።ህዝቡ የፈለገውን መርጦ ይግዛ።የግድ የኔ ሀሳብ ነው ትክክል ማለት እኔ ወያኔ ነኝ ማለት ነው።በመሆኑም ሁሉም አንድ ሁኖ የየራሱ ሀሳብ ማራመድ አለበት።ከማንም በፊት የሀሳብ ልዩነትን ተቀብለን አንድነትን የሰበክን ሰዎች ዛሬ ከራሳችን እንኳን አንድ መሆን አቃተን።

፨፨፨ህዝባችን በዚህ ሰዓት በጣም ተቸግሯል የሚደርስለት ሰው ይፈልጋል።በዚህ ሰዓት ካልደረስንለት መቼም ልንደርስለት አንችልም።

➡️በመካከላችን ያለውን ክፍተት በተመለከተ የራያ ሰላም ልማት ማህበር ቀጣይ የቤት ስራው አድርጎ ልይዘው ይገባል።

➠ራያ የሁሉም ናት።ሁሉም የራያ ሰው በራያ ጉዳይ ይመለከተዋል።

መልካም አስተዳደር የግለሰብን ሰብአዊ መብትና የዜጎችን ነፃነት የሚጠብቅ በፍትህ እና በሰላም የተመሰረተ ስርአት ለመፍጠር ቁርጠኛ የሆነ የመንግስት አካሄድ ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደገለጸው መልካም አስተዳደር የሚለካው በተሳትፎ፣ በህግ የበላይነት፣ ግልጽነት፣ ምላሽ ሰጪነት፣ መግባባት ላይ ያተኮረ፣ ፍትሃዊነት እና አካታችነት፣ ውጤታማነት እና ቅልጥፍና እና ተጠያቂነት ባሉት ስምንቱ ነጥቦች ነው።

ተሳትፎ ሁሉም ቡድኖች በተለይም በጣም ተጋላጭ የሆኑት የመንግስት ስርአቶችን በቀጥታ ወይም ወካይ ማግኘት እንዲችሉ ይጠይቃል። ይህ ደግሞ የመደራጀት እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ያላቸው ጠንካራ ሲቪል ማህበረሰብ እና ዜጎች መሆናቸውን ያሳያል።

የህግ የበላይነት የሁሉንም ዜጎች ሰብአዊ መብቶች እና የዜጎችን በተለይም አናሳ ብሄረሰቦችን ሰብአዊ መብቶች እና ነፃነቶችን በሚያስጠብቁ ገለልተኛ የህግ ስርዓቶች ምሳሌነት ነው። ይህንንም በገለልተኛ የፍትህ አካል እና ከሙስና የጸዳ የፖሊስ ሃይል ያሳያሉ።

ግልጽነት ማለት ዜጎች ውሳኔ የሚተላለፉበትን መንገድና መንገድ ተረድተው ማግኘት ይችላሉ፣በተለይ ውሳኔዎች በቀጥታ የሚነኩ ከሆነ። ይህ መረጃ ሊረዳ በሚችል እና ተደራሽ ቅርጸት መቅረብ አለበት፣በተለምዶ በመገናኛ ብዙሃን ተተርጉሟል።

ምላሽ ሰጪነት በቀላሉ ተቋማቱ ለባለድርሻ አካላት በተመጣጣኝ የጊዜ ገደብ ውስጥ ምላሽ መስጠትን ያካትታል።

Consensus Oriented በተለያዩ ፍላጎቶች፣ አመለካከቶች እና ከተለያየ ዜጋ የሚጠበቁ ነገሮች መካከል ሽምግልና በሚፈልግ አጀንዳ ይታያል። የማህበረሰቡን ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ማህበራዊ አውድ ጥልቅ ግንዛቤ በሚያሳይ መልኩ ውሳኔዎች መወሰድ አለባቸው።

ፍትሃዊነት እና አካታችነት ሁሉም የማህበረሰቡ አባላት መካተታቸው እና ጤንነታቸውን ለማሻሻል ወይም ለመጠበቅ ስልጣን እንዳላቸው በማረጋገጥ ላይ የተመሰረተ ነው፣በተለይ በጣም ተጋላጭ የሆኑትን ግለሰቦች እና ቡድኖች።

ውጤታማነት እና ቅልጥፍና የሚዳበረው የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት ዘላቂ የሆነ ሀብትን በመጠቀም ነው። ዘላቂነት ሁለቱንም ማህበራዊ ኢንቨስትመንቶችን እና የተፈጥሮ ሀብቶችን ለቀጣይ ትውልዶች መያዙን ማረጋገጥ ነው

ተጠያቂነት የሚያመለክተው ተቋማት ውሎ አድሮ ተጠሪነታቸው ለህዝብ እና አንዱ ለሌላው ነው። ይህ የመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ሲቪል ማህበረሰብ እና የግሉ ሴክተር ሁሉም ተጠሪነታቸው ለአንዱ ጭምር ነው።


የራያ የወሰንና የማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንደሚመለስ የፌዴሬሽን ም/ቤት ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የራያ የወሰንና የማንነት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንደሚመለስ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለጸ፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ለራያ ሕዝብ ተወካዮች ላቀረቡት ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ፥ የራያ ሕዝብ ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሰረት ታይቶ ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የራያ ሕዝብ ተወካዮች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የራያ ሕዝብ የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ያቀረቡ ቢሆንም ለረጅም ጊዜ ምላሽ ሳያገኝ እንደቆየ አውስተዋል፡፡

ተወካዮቹ አያይዘውም የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ሞትን ጨምሮ ሌሎች በደሎች በራያ ሕዝብ ላይ ሲፈፀም የቆየ እንደነበረና በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ራያዎች ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ እና ንብረታቸውም ሲወድም እንደነበረ ተወካዮቹ በአካል ቀርበው አስረድተዋል፡፡

ጥያቄአችን ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ሲሉም ተወካዮቹ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው ፥ ጥያቄውን ላቀረቡት የራያ የማንነትና የወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የራያ ሕዝብ ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሰረት ታይቶ ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እንደ ከዚህ በፊቱ የሕዝብን ጥያቄ በኃይል ለማፈን የሚደረግ አላስፈላጊ ጫና ከሕገ መንግስቱ የሚቃረን ስለሆነ ተቀባይነት እንደሌለው የጠቆሙት አፈ ጉባዔው ፥ የሕዝብ ጥያቄ ሕግን መሠረት በማድረግ ምላሽ በመስጠት ሕብረብሔራዊ አንድነታችንን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

[1]




!


[2] መልካም አስተዳደር

የመልካም አስተዳደር ስልጠና ፈጠራ ትምህርት በአለም አቀፍ የሰላም እና ደህንነት ተቋም (IPSI) እና Global Education Initiatives (GEI) ክፍሎች በኩል የሚያደርገው ወሳኝ አካል ነው። አይፒኤስአይ በመልካም አስተዳደር እና በተዛማጅ ርእሶች ላይ በመደበኛነት ኮርሶችን በPerctitioner Intensives እንዲሁም በአለም አቀፍ ሲምፖዚየሞች አማካኝነት ከአለም ዙሪያ የተውጣጡ ባለሙያዎችን እና ምሁራንን በማሰባሰብ ያስተምራል። IPSI የመልካም አስተዳደር ተከራዮችን ከCreative Associates ጋር አብሮ ለሰራው Fragility Resilience Assessment Method (FRAMe) እንደ ግንባታ ተጠቅሞባቸዋል። GEI ከሌሎች አገሮች የመጡ ግለሰቦች በብጁ ባበጀ የተማሪ ትምህርት እና የተለማማጅ ትምህርት ፕሮግራማቸው ስለ መልካም አስተዳደር እና ፌዴራሊዝም እንዲማሩ በየጊዜው ያስተናግዳል።[Good Governance 1]

  1. ^ ባራንቶ ኣባሴሩ
  2. ^ Good governance
  1. ^ spa raya


Cite error: <ref> tags exist for a group named "Good Governance", but no corresponding <references group="Good Governance"/> tag was found