አቢ-ኤሹሕ
(ከአቢ-ኤሹህ የተዛወረ)
አቢ-ኤሹሕ ከ1624 እስከ 1596 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የባቢሎን 8ኛ ንጉሥ ነበረ። አባቱን ሳምሱ-ኢሉናን ተከተለው።
ለአቢ-ኤሹሕ ዘመን የተለያዩ የዓመት ስሞቹ ታውቀዋል፣ ቅደም-ተከተላቸው ግን አይታወቅም። በአንዱ አመት ካሣውያን አንዳሸነፈ ይዘገባል፤ በሌላው ኤሽኑናን ድል ማድረጉን ይነገራል። በተረፈ የዓመት ስሞቹ የአረመኔነት ሕንፃዎችና ጣኦታት ስለ መሥራቱ ናቸው።
አንዱ ዜና መዋዕል ያለበት ጽላት (ABC 20) እንደሚገልጽ፣ አቢ-ኤሹሕ በኢሉማ-ኢሊ ላይ በመዘመት ጤግሮስ ወንዝን ገደበ፣ ሊይዘው ግን አልቻለም። በዘመኑም የኤላም ንጉሥ ኩቲር-ናሑንቴ ውርሮ ኤላማውያን 30 የባቢሎኒያ ከተሞች ዘረፉ።
በሌላው ጽላት «በንጉሥ አቢ-ኤሹሕ ዘመን ጊሚል-ጉላ እና ታቂስ-ጉላ መምህሮቹ ነበሩ» ይላል። የአቢ-ኤሹሕ ስም በበርካታ ሌሎች ቅርሶች ተገኝቷል።
የአቢ-ኤሹሕ ተከታይ ልጁ አሚ-ዲታና ነበረ።
ቀዳሚው ሳምሱ-ኢሉና |
የባቢሎን ንጉሥ 1624-1596 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ አሚ-ዲታና |