አሚ-ዲታና ከ1596 እስከ 1559 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የባቢሎን 9ኛ ንጉሥ ነበረ። አባቱን አቢ-ኤሹሕን ተከተለው።

ለአሚ-ዲታና ዘመን 37 የዓመት ስሞቹ ታውቀዋል። እነዚህ የዓመት ስሞች ባጠቃላይ ስለ አረመኔ ጣኦታት የሚነካ ናቸው። 17ኛው ዓመት ወይም 1579 ዓክልበ. ያህል «የ<...> ምድር ሰው ያራሕ-አቢ የያዘበት ዓመት» ይባላል። ይህ ምናልባት በዓመፃ የተነሣ አለቃ ሊሆን ይችላል። በ37ኛው ዓመት የደር ከተማ ግድግዳ እንዳጠፋ ይዘገባል።

የአሚ-ዲታና ተከታይ ልጁ አሚ-ሳዱቃ ነበረ።

ቀዳሚው
አቢ-ኤሹሕ
ባቢሎን ንጉሥ
1596-1559 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
አሚ-ሳዱቃ

የውጭ መያያዣ

ለማስተካከል