አርዋድ የሶርያ (የቀድሞ ፊንቄ) ጥንታዊ ከተማ-ደሴት ነው።
34°51′ ሰሜን ኬክሮስ እና 35°51′ ምሥራቅ ኬንትሮስ
በትንቢተ ሕዝቅኤል (27:8,11) በአማርኛ አራድ ተብሎ ይጠቀሳል፣ ይህ ከግሪክኛው ስም አራዶስ ነው። አርዋድ እጅግ ጥንታዊ ስሙ ሲሆን ለከነዓን ልጅ ለአራዴዎን (ዕብራይስጥ፦ አርዋዲ) እንደ ተሰየመ በሰፊ ይታመናል።