አውሩኑስ
(ከአሩኑስ የተዛወረ)
አውሩኑስ ጣልያናዊው መኖኩሴ አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ በ1490 ዓ.ም. ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ፣ በጣልያን ሀገር የነገሠ ንጉሥ ነበር። የክራኑስ ራዜኑስና የያኒጌና ልጅ ይባላል። በ2181 ዓክልበ. ግድም ክራኑስ ከቲቤር ወንዝ ደቡብ ባለው ክፍል ገዥ ሾመው። በ2158 ዓክልበ. ክራኑስ ሲሞት አውሩኑስ የስሜን ጣልያ («ራዜና») ንጉሥ ሆኖ ተከተለው። በ2142 ዓክልበ. ግሪፎኒ የተባለ ሕዝብ ከአርሜኒያ ወደ አውሩኑስ በራዜና መጥተው መኖሪያ ቤቶች እንደ ሰጣቸው ይላል። በ2134 ዓክልበ. ደግሞ የአውሶን መርከበኞች ከሶርያ ደርሰው በምስራቅ ጣልያን መኖሪያ ተሰጡ። በ2118 ዓክልበ. ልጁን ማሎት ታገስ የደቡብ ክፍል ገዥ አደረገው፤ በ2117 ዓክልበ. ሞተና ማሎት ታገስ ተከተለው።
ቀዳሚው ክራኑስ ራዜኑስ |
የራዜና (ጣልያን) ንጉሥ 2158-2117 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ) |
ተከታይ ማሎት ታገስ |