ደብረ አማና
(ከአማና የተዛወረ)
ደብረ አማና (ቱርክኛ፦ Nur Dağları /ኑር ዳጅላርዕ/ ማለት «የብርሃን ተራሮች») በቱርክ አገር ደቡብ ጫፍ የሚገኝ የተራራ ሰንሰለት ነው።
የአርፋክስድ ርስት እስከ ደብረ አማናና እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ እንደሚደርስ በኩፋሌ ይባላል።
የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ ስትራቦን እንደሚለን (i.2)፣ አንዳንድ የድሮ መምህሮች የጥንታዊ አይቲዮፒያን ግዛት ከደብረ አማና ጀምሮ ወደ ደቡብ (ከነሶርያ፣ እስራኤልና ዓረብ ሁሉ) ይቆጥሩት ነበር።
በ2038 ዓክልበ. ግድም የአካድ ንጉሥ ናራም-ሲን ኤብላን ከያዘ በኋላ በአማናና በሊባኖስ ዙሪያ ዘመተ።