ኔፓል ባሳ
ኔፓል ባሳ ወይም ነዋሪኛ (नेपाल भाषा) በኔፓል የሚነገር ቋንቋ ነው። በቻይናዊ-ቲቤታዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ውስጥ ካሉት ቋንቋዎች መካከል እሱ ብቻ በዴቫናጋሪ አቡጊዳ የሚጻፈው ነው። ነዋር ከተባለ ነገድ የሆኑት 1 ሚልዮን ያሕል ሰዎች ይችሉታል። የቻይንኛና የቲቤትኛ ዘመድ ቢሆንም ከሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ከፍ ያለ ተጽእኖ ተቀብሏል።
በታሪክ መዝገብ ከሁሉ የቆየ ጽሕፈት በኔፓል ባሳ ከ1122 የታወቀው 'የኡኩ ባሃል ዘምባባ ቅጠል' ነው።
ዛሬ ኔፓል ባሳ ጋዘጣዎች፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት፣ በራዲዮና በቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ የተወሰነ መደብ፣ አንዳንድም ዌብሳይት ይገኛሉ። ነገር ግን በቅርቡ ዘመናት የኔፓል መደበኛ ቋንቋ ኔፓል ባሳ ሳይሆን ኔፓልኛ (አንድ የህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች አባል) ስለ ሆነ፣ የኔፓል ባሳ ሁኔታ ወደ ታች ወርዷል።
ምሳሌ ቃላትና ዘይቤዎች
ለማስተካከል- ታዲያስ - ጇጃላፓ
- ስምዎ ማን ነው? - ጪጉ ና ጩ ሐ?
- መልካም ዕንቁጣጣሽ - ንሑጉ ዳን ያ ቢንቱና
- ጓደኛ - ፓሳ
- ድርጅት - ጉጢ
- ቤት - ጨን
- ሰው - ማኑ
- መድኃኒት - ዋሳ
- ዜና - ቡሐን
- ጭፈራ - ፕያሐን
- ቢሮ - ጅያሳ
- ሱቅ - ፓሳል
- ግቢ - ቹካ
- አዕምሮ - ነፑ
- ልብ - ኑጋህ
- ውኃ - ና፣ ላህ
- ኔፓል ባሳ አይገባኝም - ጂታ ኔፓል ባሳ ማዋ
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |