ዌብሳይት በአንድ ዌብ ሰርቨር ላይ የሚገኙ የጋራ የሆነ የጎራ ስም ያላቸው ድረ ገጾች ስብስብ ነው። ዌብሳይቶች አብዛኛው ጊዜ index የሚባል የማውጫ ገጽ አላቸው። የአንድ ዌብሳይት አድራሻ ብቻ ሲጻፍ (ምሳሌ፦ www.wikipedia.org) ይህ የማውጫ ገጽ ይላካል።

ሁሉም ለህዝብ ክፍት የሆኑ ዌብሳይቶች በጥቅል ወርልድ ዋይድ ዌብ ይመሰርታሉ ማለትም ፌስቡክ፣ ጉግል፣ ዊኪፔዲያ ሁሉም ለህዝብ ክፍት ስለሆኑ በወርልድ ዋይድ ዌብ ውስጥ ይገኛሉ። ሌሎች ለህዝብ ክፍት ያልሆኑ ዌብሳይቶችም አሉ እነዚህ በግል ኔትዎርክ ተጠቅመን ምናገኛቸው ናቸው። ለምሳሌ ለአንድ ድርጅት ሰራተኞች ብቻ ነተሰራ ዌብሳይት።