ናዝሬት ወዲህ ይመራል። ለእስራኤል ከተማ፣ ናዝሬት፣ እስራኤልን ይዩ።

ኣዳማ በአማርኛ ናዝሬትኦሮሚያ ክልል ለኦሮሚያ በዋና ከተማነት የሚያገለግል የኢትዮጵያ ከተማ ነው። በምስራቅ ሸዋ ዞን በላቲቱድና ሎንጂቱድ 8.55° N 39.27° E ላይ ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ ምዕራብ 100 ኪሎመትር ላይ ይገኛል።

አንድ ጋሪ የአዲስ አበባ-ድሬዳዋ መንገድ ሲያቋርጥ።

እንደ ሲቲ ፖፑሌሽን መረጃ  አዳማ ከተማ የ456,868  ሰዎች መኖሪያ ስትሆን ሲሆን ከኗሪዎቿ 223,560  ወንዶችና 233,308 ሴቶች ናቸው።[1]

አዳማ በትራንስፖርት ማእከልነት የታወቀ ከተማ ነው። ከተማው በአዲስ አበባና በድሬዳዋ መንገድ ላይ ይገኛል። አዲስ አበባ ጅቡቲአሰብ (ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በፊት ኢትዮጵያ አሰብን ስትጠቀም) የሚመላለሱ ቁጥራችው ከፍ ያሉ የጭነት መኪኖች የሚያልፉት በአዳማ ነው። ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ የሚሄደው ምድር ባቡርም አዳማን ያቋርጣል።


  1. ^ https://www.citypopulation.de/en/ethiopia/admin/oromia/ET040714__adama