ነፋስ መውጫ በደቡብ ጎንደር የሚገኝ፣ የላይ ጋይንት ወረዳ ዋና ከተማ ነው። ከደብረ ታቦር ወደ ወልደያ በሚጓዘው መንገድ ላይ በመገኘቱ፣ እንዲሁም በአካባቢው በሚገኙት ጥንታዊ ገዳሞች ጋይንት ቤተልሔም እና ውቅሮ መድሃኒ አለም ታዋቂነትን ያገኛል።

ነፋስ መውጫ
ነፋስ መውጫ ከተማ
ከፍታ 3120 ሜትር
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 18,691
ነፋስ መውጫ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ነፋስ መውጫ

11°44′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°28′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

ታሪክ ለማስተካከል

በ1612 ዓ.ም. ዓፄ ሱሰኒዮስ በጠላታቸው ዮናኤል ላይ ዘመቻ ሲያካሂዱ እዚህ ከተማ ለጊዜው እረፍት እንዳደረጉ ዜና መዋዕላቸው ያትታል[1]

ከ150 አመት በኋላ ወደዚህ አከባቢ የተጓዘው ስኮትላንዳዊው ሐኪም ያዕቆብ ነፋስ መውጫ የድሮው በጌምድር ግዛት ደቡባዊ ምስራቅ ጠርዝ እንደሆነ ዘግቦት ይገኛል[2][3]። በዓፄ ኢዮአስ የግዛት ዘመን መገባደጃ የአጠቃላይ በጌምድር አስተዳዳሪ የነበረው የማሪያም ባሪያው ቤቱን ነፋስ መውጫ አካባቢ ሰርቶ ይኖር እንደነበር ብሩስ ይተርካል። ሆኖም በንጉሱ አጎት፣ ደጅአዝማች ብርሌ ቆስቋሽነት በተነሳ ጦርነት የማርያም ባሪያው ደጃማች ብርሌን እንደገደለው ይጠቀሳል። በዚህ ምክንያት የንጉሱ ሠራዊት፣ የራስ ሥዑል ሚካኤል እና ወረኛ ፋሲል ጦር አንድ ላይ በመሆን የማርያም ባሪያውን ነፋስ መውጫ ላይ እንደወጉት፣ በኋላም የማርያም ባሪያው ስለቆሰለ ወደ ወሎ እንደሸሸ፣ የወሎ ኦሮሞ አባላት ይዘው ለንጉሱ እንዳስረከቡት እና በኋላም እንደተገደለ ብሩስ ይዘረዝራል[4][5]

በ1940ዎቹ ከደብረታቦር ወደ ምስራቅ የተዘረጋው የስልክ መስመር እዚህ ከተማ ያቆም ነበር። በ1956ዓ.ም.፣ ነፋስ መውጫ፣ የጋይንት አውራጃ ዋና ከተማ ነበር። በ1960 ዓ.ም. የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቱ 231 ወንዶችና 132 ሴት ተማሪዎች 9 አስተማሪዎች፣ እንዲሁም መካከለኛ ደረጃ ትምህርትቤት ውስጥ የሚማሩ 64 ወንዶች፣ 13 ሴቶችና ሁለት ኢትዮጵያዊ አስተማሪዎች ነበሩት[6]። ጥር 5፣ 1982 ዓ.ም. ከተማው በደርግ የጦር አውሮፕላኖች ተደብድቦ 23 ግለሰቦች ተገደሉ[7]

የሕዝብ ስብጥር ለማስተካከል


ማጣቀሻ ለማስተካከል

  1. ^ የአጼ ሱሰንዮስ ዜና መዋዕል
  2. ^ G.W.B. Huntingford, The historical geography of Ethiopia from the first century AD to 1704, (Oxford University Press: 1989), p. 174
  3. ^ በኢንተርኔት
  4. ^ Bruce, Travels, vol. 4 pp. 177f
  5. ^ ኢንተርኔት1
  6. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2011-06-13. በ2011-12-15 የተወሰደ.
  7. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2011-06-13. በ2011-12-15 የተወሰደ.