ቼክ
- ለሀገሩ፣ የቼክ ሪፑብሊክ ይዩ።
ቼክ ከቼኪንግ አካውንት ውስጥ የተቀመጠን ገንዘብ በመጠቀም እቃ ወይንም አገልግሎት ለመግዛት የሚጠቅም መሳሪያ|ዶሴ ነው። ቼኮች ምንጊዜም ራውቲንግ ቁጥር እና አካውንት ቁጥር አላቸው። ራውቲንግ ቁጥሩ የቼክንግ አካውንቱ የት ባንክ ውስጥ እንደሚገኝ ሲያሳይ፣ አካውንት ቁጥሩ ደግሞ በዚያ ባንክ ውስጥ ያ አካንት የማን እንደሆነ ያሳያል።
ቼክ ለመጻፍ (በቼክ ለመክፍል) ፣ ቀኑን፣ የከፋዩን ስም፣ የተከፋዩን ስም፣ የሚከፈለውን ገንዘብ ብዛት፣ በአሃዝ እና በፊደል መጻፍ ይገባል። በመጨረሻም ከፋዩ ሰው ቼኩን መፈረም ይኖርበታል።
የቼክ ጥቅም፡ ጥሬ ገንዘብ ይዞ ከመዞር ያድናል። በፖስታ ቤት ክፍያን ለመላክ ይረዳል።
የቼክ መጥፎነት፡ ክፍያው ቅጽበታዊ አይደለም። ትናንሽ ክፍያወችን ለመክፈል አያስችልም። ካለ ገንዘብ በላይ ለማውጣት ያስችላል።