ቹምቢ ሸለቆቲቤት (ቻይና) ውስጥ የሚገኝ ሸለቆ ሲሆን በሲኪም (ሕንድ)፣ ቡታንና ቲቤት መገናኛ ቅርብ ነው። በረጃጅሞች ሂማላያ ተራሮች መካከል የሚያሳልፉ ሥፍራዎች በአካባቢው አሉ።

ቹምቢ ሸለቆ በ1930 ዓም

ሸለቆው በእንግሊዝ ኃይላት ከ1896 ዓም እስከ 1900 ዓም ድረስ ተያዘ፤ የ1896ም ወረራ መጀመርያ መትረየስ የተጠቀመበት ዘመቻ ነበረ። ይህ መሬት የቲቤት ክፍያ በ1900 ዓም ከቻይና ጪንግ መንግሥት እስከሚገኝ ድረስ ተያዘ።