ትራንስፖርት ምህንድስና
የቀለም ትምህርት እና የስራ ዘርፍ
የትራንስፖርት ምህንድስና ሰዎችንና ቁሳቁስን ከቦታ ወደ ቦታ በደህንነት ፣ በተቀላጠፈና ምቹ በሆነ መንገድ ማጓጓዝ ላይ ትኩረት ያደርጋል። ይህንን አላማማ ለማሳካትም የመኪና፣ የባቡር፣ የውሃና የአየር ማረፊያ መንገዶች እንዲሁም የወደቦች ንድፍ፣ ግንባታና ጥገና ስራዎች በትራንስፖርት ምህንድስና ውስጥ ሰፊ ድርሻ ይይዛሉ። የትራንስፖርት ምህንድስና በውስጡ የትራንስፖርት ንድፍ ስራ (transportation design) ፣ የትራንስፖርት ግንባታ እቅድ (transportation planning)፣ የትራፊክ ምህንድስና (traffic engineering)፣ የከተማ ልማት ምህንድስና፣ የመንገድ ንጣፍ ምህንድስና የመሳሰሉ ንኡስ የሙያ ዘርፎችን የያዘ ነው።