ታልሙን
ታልሙን (ኮሪይኛ፦ 달문) በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ (ጎጆሰን) የነገሠ ንጉሥ ወይም «ዳንጉን» ነበር። እርሱ ከዳንጉን ጉዕል መንግሥት ቀጥሎ ገዛ። ታልሙን ከጉዕል ፭ ሚኒስትሮች «ዉጋ» የተባለው ነበር።
በጠቅላላ ለ፴፮ ዓመታት(ምናልባት 1865-1830 ዓክልበ.) እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ ሃንዩል ተከተለው።
በኋንዳን ጎጊ
ለማስተካከልበ1903 ዓም. በኮሪይኛ የተዘጋጀው ዜና መዋዕል ኋንዳን ጎጊ ስለዚሁ አፈታሪካዊ ዘመን መረጃ ይሰጣል፤ ሆኖም በብዙ የኮርያ መምህሮች ዘንድ ይህ መጽሐፍ እንደ ትክክለኛ ታሪክ አይሆንም። ስለ ዳንጉን ታልሙን ዘመን የሚከተለው ብቻ ይለናል፦
- በ1831 ዓክልበ. ግድም ታልሙን የነገዶቹን አለቆች በሳንግቹን አሰበሰባቸው፤ መስዋዕት ለሰማያት ከሠዋ በኋላ ሚኒስትሩን ባዓሊ የመሐሌ ድርሰት እንዲጽፍ አዘዘው። ይህ ድርሰት ስለ ቺ ዮው ይተርካል፤ በመጨረሻም «ግብረገብ ምንጊዜም እንደ ጎንዛላ ሣር ይታደስ። ቅሬታ ያለው ቂሙን አይበቅል» የሚል ነው። በዚህ ወቅት፣ ፪ ትላላቅ ክፍላገራት፣ ፳፪ ትንንሽ ክፍላገራትና 3,624 መንደሮች በታልሙን መንግሥት ተቆጠሩ።
በሚከተለው ዓመት ታልሙን ዓረፈና ሚኒስትሩ ሃንዩል ተከተለው።
ቀዳሚው ጉዕል |
የጆሰን ዳንጉን | ተከታይ ሃንዩል |