ሃንዩል (ኮሪይኛ፦ 한율) በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ (ጎጆሰን) የነገሠ ንጉሥ ወይም «ዳንጉን» ነበር። እርሱ ከዳንጉን ታልሙን መንግሥት ቀጥሎ ገዛ። ሃንዩል ከታልሙን ፭ ሚኒስትሮች «ያንጋ» የተባለው ነበር።

በጠቅላላ ለ፶፫ ዓመታት(ምናልባት 1830-1778 ዓክልበ.) እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ ሰውሃን ተከተለው።

1903 ዓም. በኮሪይኛ የተዘጋጀው ዜና መዋዕል ኋንዳን ጎጊ ስለዚሁ አፈታሪካዊ ዘመን መረጃ ይሰጣል፤ ሆኖም በብዙ የኮርያ መምህሮች ዘንድ ይህ መጽሐፍ እንደ ትክክለኛ ታሪክ አይሆንም። ስለ ዳንጉን ሃንዩል ዘመን ግን ዘውድ ከመጫኑና ከማረፉ በቀር ምንምን ድርጊቶች አይዘገብም።

ቀዳሚው
ታልሙን
ጆሰን ዳንጉን
1830-1778 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሰውሃን

ዋቢ ምንጭ ለማስተካከል