ተረት ጸ
- ጸሀይ ሳለ ሩጥ አባት ሳለ አጊጥ
- ጸሀይ ብልጭ ወፍ ጭጭ ሲል
- ጸሀይ ካልወጣ ከሰፈረበት አይነሳ አንበጣ ሴት ምክንያት አታጣ
- ጸሀይ የጠዋት አዱኛ የሽበት
- ጸሀይ ያየውን ሰው ሳያየው አይቀርም
- ጸሀይና ንጉስ ሳለ ሁሉም አለ
- ጸሎት በጽሞና ነገር በደመና
- ጸሎት በፍቅር ሀይማኖት በምግባር
- ጸሎት ከፍቅር ሀይማኖት ከምግባር ይበጃል
- ጸሎት ከፍቅር ሀይማኖት ከግብር
- ጸሎት ያለፍቅር ሀይማኖት ያለግብር አይረባም
- ጸጸት እያደር ይመሰረት
- ጻድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ
- ጻድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ ሀጥአን ግን በተቃጠሩበት ይተጣጣሉ
- ጽዋ በተርታ ስጋ በገበታ
- ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ
- ጽድቁ ቀርቶብኝ በውሉ በኮነነኝ
- ጽድቅ ለመንኳሽ ቀኝ ለከሳሽ
- ጽድቅ እንደ ላሊበላ እድሜ እንደ ማቱሳላ ይስጥህ
- ጽህፈት በብራና ዘፈን በበገና
- ጾማ ጾማ ለጸሎተ ሀሙስ እርጎ ትልስ
- ጾም ገዳፊና ሰው ጠባቂ ለጥቂት ይሳሳታል