ተረት ነ
]]
- ነቅናቂ ሳለ ማን ጥሩ ይጠጣል
- ነበረ እንጂ ይኖራል የሚባል ፍጡር የለም
- ነበርንበት አትኩሩበት
- ነቢያት በመደመዱ ሀዋርያት ገደገዱ
- ነቢያት በቀየሱ ሀዋርያት ገሰገሱ
- ነቢይ ቢኖር በከበረ ነበር
- ነቢይ ባገሩ አይከበርም
- ነብር ቢያንቀላፋ ዝንጀሮ ጎበኘው
- ነብር ባየለበት ዘመን ድመት ይበረታል
- ነብር ባየለበት ዘመን ድመት ይኮርታል
- ነብር ሳይገድል ቆዳውን ያስማማል
- ነብር አየኝ በል
- ነብር አይኑን ታመመ ፍየል መሪ ሆነ
- ነብር የሞተ እለት ፍየል ልጅዋን ትድራለች
- ነዋሪ ለዘላለም አለ አምላክ የለም
- ነውር ለባለቤቱ እንግዳ ነው
- ነገረኛ ሰው ከቤቱ አይሞትም
- ነገረኛ ታሞ አይተኛ
- ነገረኛ ናቸው አርቃችሁ ቅበሩዋቸው
- ነገረኛ ናቸው አጥልቃችሁ ቅበሩዋቸው የተነሱ እንደሆን ብዙ ነው ጣጣቸው
- ነገረኛ ዝንጀሮ ውሻ ታረባለች
- ነገሩ ነገር ነው ውስጡ ጥቅንጥቅ ነው
- ነገሩ ነገር ነው ውስጡ ጉራንጉር ነው
- ነገሩ ነው እንጅ ቢላዋ ሰው አይጎዳም
- ነገሩ ነው እንጅ ጩቤ ሰው አይጎዳም
- ነገሬ በሆዴ መንገዴ ባመዴ
- ነገሬ በከንፈሬ
- ነገር ለበለጠ ውድማ ለመለጠ
- ነገር ለበለጥ ውድማ ለመለጥ
- ነገር ለሰሚ ውሀ ለሎሚ
- ነገር ለጀማሪው እሳት ለጫሪው
- ነገር ሲበዛ ይሆናል ዋዛ
- ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ
- ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም
- ነገር ሲያመልጥ እራስ ሲመልጥ አይታወቅም
- ነገር ሲጀመር እህል ሲከመር
- ነገር ሳያውቁ ሙግት ሳይጎለብቱ ትእቢት
- ነገር ሳያውቁ ሙግት አቅም ሳይኖር ትእቢት
- ነገር ስንት ነው ሁለት ምን ያበዛዋል ውሸት
- ነገር በሆዴ መንገድ በአመዴ
- ነገር በሆዴ እየተመኘሁ ቢከፍቱት ተልባ ሆኜ ተገኘሁ
- ነገር በለዛው ጥሬ በለዛዛው
- ነገር በልክ ሙያ በልብ
- ነገር በመልከኛ ጠላ በመክደኛ
- ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ
- ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ መዝሙር በሀሌ
- ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ዜማ በሀሌ
- ነገር በቀጠሮ ዘፈን በከበሮ
- ነገር በትኩሱ ጨዋታ በወዙ
- ነገር በነገር ይጠቀሳል እሾህ በእሾህ ይነቀሳል
- ነገር በእርቅ መንገድ በድርቅ
- ነገር በእርቅ ወይፈንን በድርቅ
- ነገር በወቀሳ በደል በካሳ
- ነገር በዋስ እህል በነፋስ
- ነገር በዋና ሚዶ በእረኛ
- ነገር በዋና ሜዳ በእረና
- ነገር በዋና ዘፈን በገና
- ነገር በዋናው ንብ በአውራው
- ነገር በዳኛ ሚዶ በእረኛ
- ነገር ቢሳሳት ከጥንቱ ሰይፍ ቢመዘዝ ካፎቱ
- ነገር ቢሳሳት ከጠዋቱ ጥጃ ቢሳሳት ከእናቱ
- ነገር ቢበዛ ባህያ አይጫንም
- ነገር ባዋቂ ብረት በጠራቂ
- ነገር አለኝ ከማለት ስራ አለኝ ማለት
- ነገርን አድምጦ እህልን አላምጦ
- ነገር እንደዛፉ ዛፉ እንደቅርንጫፉ
- ነገር ከመጀመሪያው እህል ከመከመሪያው
- ነገር ከመጀመሪያ ፍለጋ ከመሻገሪያ
- ነገር ከመጀመሪያው ውሀ ከመሻገሪያው
- ነገር ከስነበተ ቅራሪ ከሆመጠጠ
- ነገር ካምጩ ውሀ ከምንጩ
- ነገር ከስሩ ውሀ ከጥሩ
- ነገርን ከስሩ ውሀን ከጥሩ
- ነገር ከእብድ ይገኛል
- ነገር ከእጅ ይገኛል
- ነገር ከዋስ ምላስ ከጥርስ
- ነገር ከዋስ ምላስ ከጥርስ አያልፍም
- ነገር ከውሉ ጋሻ ከንግቡ
- ነገር ከግቡ ጋሻ ከእንግቡ
- ነገር ከፊቱ ዱቄት ከወንፊቱ
- ነገር ካንሹ ስጋ ከጠባሹ
- ነገር ካንሺው ስጋ ከጠባሺው
- ነገር ካጀማመሩ እሀ ል ካከማመሩ
- ነገር ወዳድ ሰው ከመንገድ ዳር ቅበሩኝ ይላል
- ነገር ወዳጅ ሰው ከመንገድ ዳር ቅበሩኝ ይላል
- ነገር ወዳጅ ከቤቱ አይሞትም
- ነገር ወዴት ትሄዳለህ ጎንደር መጨረሻህ ታገር
- ነገር ያለዳኛ ትብትብ ያለመጫኛ
- ነገር የሚከረው ጎንጓኙን ሲያገኝ ነው
- ነገር የሻ ዳኛ አምጡ ይላል የዶሮ ሻኛ
- ነገር የዋለበት ዳኛ ያውቃል ከብት የዋለበት እረኛ ያውቃል
- ነገር የፈራ ይቃጠራል አውሬ የፈራ ያጥራል
- ነገር ያለዳኛ ተረት ሰማይ ያለ ደመና ብረት
- ነገር ፈጣሪውን እሾህ አጣሪውን
- ነገር ነገርን ያነሳል ጥጋብ ሞትን ያስረሳል
- ነገርህና ነገሬ ልክ ነው ሰው መስማቱ ትርፍ ነው
- ነገር ነገርን ያመጣል ድግር አፈር(ን) ያወጣል
- ነገርህን በጠጄ ርስትህን በልጄ
- ነገር በነገር ይወቀሳል እሾህ በሾህ ይነቀሳል
- ነገርም ይበረክታል ባለጋራም ይታክታል
- ነገርኩት መስዬ እንዲመስለው ብዬ
- ነገር መጫኛ እንዳሳጠሩት ወይም እንዳስረዘሙት ነው
- ነገርና ገመድ አለውሉ አይፈታም
- ነገርን በእርቅ ወይፈንን በድርቅ
- ነገር እንዲጠፋ ዳኛውን ግደል
- ነገር ነገርን ይወልዳል
- ነጋሪ የሌለው ይታማ አይመስለው
- ነጋዴ ወረቱን ዘላን ከብቱን ገበሬ ምርቱን
- ነጋዴን ተዘማች ምን አቀላቀለው
- ነጻነት ያኮራል ስራ ያስከብራል
- ነጭ ሽንኩርት በመሽተቱ እራሱን ቀብሮ ይኖራል
- ነጭ ድሀ ነጭ ማር ይከፍላል
- ነጭ እንደሸማ ትክል እንደትርሽማ
- ነጭ እንደሸማ ትክል እንደአክርማ
- ነፋስ በተነሳበት ጊዜ እሳት አይጭሩም
- ነፋስ ሲነሳ እሳት አይጫርም
- ነፍጥ ቢያጓራ የጌታውን ጎን ይሰብር
- ነፍጥ ቢያጓር የጌታውን ጎን ይሰብር
- ነፍስ በፈጣሪዋ ሴት ባሳዳሪዋ
- ኑር ባገር ጥፋ ካገር
- ኑሮ በዘዴ አቶ ዘወልዴ
- ኑሮ በዘዴ ጾም በሁዳዴ
- ኑሮ በደጋ መተኛት ባልጋ
- ኑሮ ቢያምርህ ችላ ጥጋብ ቢያምርህ ባቄላ
- ኑሮ ከማናደድ ሄዶ መመስገን
- ኑሮ ከማናደድ ሄዶ መናፈቅ
- ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል
- ኑሮ ካሉት የጤፍ ቅጠል ሁለት ሰው ያስተኛል
- ኑሮ ካሉት ፍሪጅ ይሞቃል
- ኑሮ ካሉት ፍሪጅ ይሞቃል አለ የቢራ ጠርሙስ
- ኑ ባይ ከባሪ እንቢ ባይ ቀላይ
- ኑሮ ኑሮ ከመሬት ዙሮ ዙሮ ከቤት
- ኑሮ ኑሮ ከመሬት ዙሮ ዙሮ ከቤት አይቀርም
- ኑሮ ያኗኑራል ህግ ያከባብራል
- ናቂ ወዳቂ
- ና ብላ ሳይሉት ከወጡ አውጡልኝ
- ና ያሉት እንግዳ እራቱ ፍሪዳ
- ናዳ መጣልህ ቢሉት ተከናንቤአለሁ አለ
- ናዳ መጣልህ ቢሉት ተከናንቤአለሁ ልቀቀው አለ
- ንቡን አባሮ ማሩን
- ንብ ላጥር ሳያረዳ አይሄድም
- ንብ ሲሰማራ አጥሩን ተመልከት
- ንብ ቢሄድ ካጥር ሰው ቢሄድ ካገር
- ንብ ቢሄድ ካጥር ሰው ቢሰደድ ካገር
- ንብ ባውራው ገበሬ ባዝመራው
- ንብን አይተህ ተገዛ ብሎዋል እግዜር
- ንካ ያለው አይቀርም
- ንዳማ ቢአጭዱት ክምር አይሞላም
- ንጉሱ በድንኳናቸው እኔ በጎጆዬ
- ንጉሱ በድንኳናቸው እኔ በጎጆዬ ንጉስ ነን አለ ድሀ
- ንገስ ቢሉት ሳልዋጋ አልነግስ አለ
- ንጉስ ለብያኔ አቡን ለኩነኔ
- ንጉስ በመንግስቱ እግዜር በመለኮቱ ጎልማሳ በሚስቱ
- ንጉስ በመንግስቱ ጎልማሳ በሚስቱ አምላክ ባምላክነቱ
- ንጉስ በግንቡ ይታማል
- ንጉስ በግንቡ ገበሬ በርስቱ ቢገቡባቸው ቀናተኞች ናቸው
- ንጉስ ከግንቡ ውጭ ይታማል
- ንጉስ በዘውዱ ድሀ ባመዱ
- ንጉስ ቢቆጣቀስ ብለህ ውጣ
- ንጉስ ሲቆጡ ቀስ ብላችሁ ውጡ
- ንጉሱ ቢሞቱ ከማን ይሟገቱ
- ንጉስ ቢያተርፍ ሁሉ ይተርፍ
- ንጉስ ሲሞት ግንቡን ብልህ ሲሞት ልቡን
- ንጉስ አንጋሹን ቤተክርስቲያን ቀዳሹን
- ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ
- ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ አባት አይወቀስ
- ንጉሱ ከሾመው ማረሻ የሾመው
- ንጉስ ከተነፈሰ አይን ከፈሰሰ
- ንጉስ ከተነፈሰ ውሀ ከፈሰሰ
- ንጉስ ይተክላል ንጉስ ይነቅላል
- ንጉስ የቆረጠው እጅ ካለ ይቆጠራል
- ንጉስ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት
- ንጉስ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት (አንድ ነው)
- ንጋትን ዶሮ ያውቃል ወፍ ያረጋግጣል
- ንጋትን አውራ ዶሮ ያውቃል ወፍ ያረጋግጣል
- ንጋትና ጥራት እያደር ይታያል
- ንጉስ የሰቀለው አንበሳ የሰበረው
- ንፉግ ለግሶ ቢሰጥ እጁ ይንቀጠቀጥ
- ንጉስ የወደደው ዘመን የወለደው
- ንጉስ ያላቸው ንቦች ማር ይበላሉ ንጉስ የሌላቸው ዝንቦች ጥንብን ይልሳሉ
- ንጉስ ይሞግትልህ ንጉስ አይሞግትህ
- ንግግር ሲበዛ ይጠፋል ማር ሲበዛ ያስተፋል
- ንፍጥ ለባለቤቱ ቅቤ ነው
- ኖረሽ አልጠቀምሽን ሞተሽ አለቀቅሽን
- ኖሮ ኖሮ ከሞት ዞሮ ዞሮ ከቤት
]] ]]]]]]