ባዛያአሦር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ለ28 ዓመታት (ከ1623 እስከ 1596 ዓክልበ. ገደማ) የአሦር ንጉሥ ነበረ።

የቀድሞው ቤሉ-ባኒ (1672-1662 ዓክልበ.) ልጅ ይባላል፤ የቤሉ-ባኒ ሦስት ተከታዮች ሊባያ1 ሻርማ-አዳድኢፕታር-ሲን ሁሉ ከአባት ወደ ልጅ እንደ ወረሱ ስለሚባል፣ ይህ አጠያያቂ ነው። ስለዚሁ ዘመን ግን አንዳችም ተጨማሪ መረጃ አይታወቅም።


የሚከተለው ንጉሥ ሉላያ በዝርዝሩ ላይ «የዲቃላ ልጅ» ስለሚባል፣ ዘውድ ነጣቂ እንደ ሆነ ይታስባል። ከሉላያ 6 ዓመታት ዘመን በኋላ ግን የባዛያ ልጅ ሹ-ኒኑዓ ንጉሥ እንደ ሆነ ይላል።

ቀዳሚው
ኢፕታር-ሲን
የአሦር ንጉሥ ተከታይ
ሉላያ