ሹ-ኒኑዓ
ሹ-ኒኑዓ በአሦር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ለ14 ዓመታት (ከ1590 እስከ 1576 ዓክልበ. ገደማ) የአሦር ንጉሥ ነበረ። አንዳንድ ዘመናዊ ሊቃውንት ስሙን «ኪዲን-ኒኑዓ» ብለው ያንብቡታል።
ሹ-ኒኑዓ የባዛያ ልጅ ሲባል ቀዳሚው ሉላያ «የዲቃላ ልጅ» ወይም «የማንም ልጅ ያልሆነ» ይባላል፤ ስለዚህ ሉላያ ነጣቂ ወይም እንደራሴ እንደ ነበር ይታስባል።
የሹ-ኒኑዓ ተከታይ ልጁ 2 ሻርማ-አዳድ እንደ ነበር ይላል። ከዚህ ዘመን ምንም ሥነ ቅርስ ወይም ሌላ መረጃ የለንም።
ቀዳሚው ሉላያ |
የአሦር ንጉሥ | ተከታይ 2 ሻርማ-አዳድ |