ቢግ ማክ
ቢግ ማክ የሃምበርገር ዓይነት ሲሆን በፈጣን ምግብ ቤቱ ማክዶናልድስ የሚሸጥ ነው። ሃምበርገሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው በ1960 ዓ.ም. በአሜሪካዊው ጅም ዴልጋቲ ነበር። ሁለት የተፈጨ የበሬ ስጋ ክቦችን፣ ሰላጣ ቅጠል፣ ዓይብ፣ ሽንኩርት፣ ፒክልስ እና ሶስት የሰሊጥ ጠፍጣፋ ዳቦዎችን ከማዋዣ የቢግ ማክ ሶስ (መረቅ) ጋር ይይዛል።
ቢግ ማክ በአሁኑ ዘመን በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነት በማግኘቱ ዘ ኢኮኖሚስት የተሰኘው የሥነ ንዋይ ጋዜጣ በያመቱ ቢግ ማክ ኤንዴክስ የተባለ መረጃ ያትማል። ቢግ ማክ በያገሩ የሚሸጥበትን ዋጋ በማዎዳደር፣ የየአገሩን የኑሮ ውድነት ለማነጻጻር ይጠቀምበታል።