በር:ፍልስፍና/የተመረጠ ፈላስፋ/47
ፍሬደሪክ ዊልሄልም ኒትሸ (ኦክቶበር 15, 1844 - ኦገስት 25, 1900) ጀርመናዊ ጻህፊና ፈላስፋ ሲሆን አለምን ይቀይራሉ ብሎ ያመነባቸውን ብዙ መጻህፍት በመድረስ ይታወቃል። እርግጥ ኒሺ፣ በነበረበትም ሆነ በኋላ ዘመኑ ብዙ ተቃዋሚወች ቢነሱበትም በዚያው ልክ ብዙ ሰወች ስራወቹን እንደ ታላቅ የፍልስፍና እና ስነ ጽሁፍ ስራ ይወስዷቸዋል።
እምነቶች
ለማስተካከልኒትሸ አብዛኛው ጽሁፉ የሚያተኩረው ሰወች እንዴት ሊኖሩ ይገባቸዋል? በሚለው ጥያቄ ነው። በዚህ ምክንያት እሱ ይኖርበት የነበረውን ዘመን የጀርመን ሥነ ምግባር (ኤቲክስ) በመንቀፍ ብዙ ጽፎአል። ሠናይ እና እኩይ (ጥሩና መጥፎ) ተብለው ተለይተው ይሰራባቸው የነበሩትን የጊዜውን ሥነ ምግባር ዋጋወች በመተቸት ሰወች አዲስ ሥነ ምግባር ፈጥረው ለሁሉም ምግባር አዲስ የሠናይነትና እኩይነት (ጥሩ እና መጥፎ) ዋጋ እንዲሰጡ በጽሑፎቹ ብዙ ሞክሯል።በዚህ መሰረት፣ ለምሳሌ፣ በክርስቲያኖች ዘንድ የሚሰራበትን ለደካሞች ማዘንን ሠናይነት ተቃውሟል። በሱ አስተያየት ደካሞች ሲታዘንላቸው የበለጠ ይዳከማሉ የሚል ነው ምክንያቱም በሱ አስተያየት ደካሞቹ በጠንካሮቹ ላይ የበለጠ ጥገኛ በመሆን መላው ህብረተሰብ ይዳከማል የሚል ነው።
በተጨማሪም፣ የሰው ልጅ የሚኖርበትን ተጨባጩን አለም መገንዘብ እና ክሁሉ በላይ ስለዚሁ ዓለም ማተኮር አለበት ብሏል። ሰማይና ሌሎች አለማትን በማጣጣል፣ የሰው ልጅ እነዚህን አይነት አለሞች የሚፈጥረው አሁን ያለበትን ተጨባጩ የውኑ አለም ችግሮች መፍታት ሲያቅተው ለመፈርጠጥ ነው በማለት የሰው ልጅ ስለዚህ ምድር ብቻ እንዲያስብ ይወተውታል።
ኒሽ የሰው ልጅ እራሱን በራሱ ማሸነፍ እንዲችል አጥብቆ ያምናል። በኒሺ ፍልስፍና፣ አንድ እራሱን ያሽነፈ ሰው በጣም የተለወጠ እና የተሻለ ስለሚሆን "ሱፐር ማን" ወይም "የበላይ ሰው" እንዲባል ሰይሟል። የበላይ ሰው እንግዴህ ጠንካራና በሌሎች ሰወች "ሠናይ" እና "እኩይ" ወይም ደግሞ "ጥሩ" ና "መጥፎ" ዋጋወች የማይመራ፣ ይልቁኑ የራሱን ሥነ ምግባር የሚፈጥር ነው። .
ዋና ዋና ሓሳቦቹ
ለማስተካከል
« የሰው ልጅ ብዙ ውሸት የሚዋሸው ለራሱ ነው፣ ለሌላ ሰው የሚናገረው ውሸት በአንጻሩ ኢምንት ነው!» |
— ፍሬድሬርክ ኒትሸ |
የኒሽ ትጽኖ
ለማስተካከልየናዚ ጀርመን መሪ የነበረው ሂትለር የኒሽን ጽሁፍ ያነብ እንደነበር ታሪክ የሚያውቀው ሲሆን፣ ምንም እንኳ አንድ አንድ ሰወች እንደሚሉት የኒሽን ስራ ሂትለር የመረዳት አቅሙ ባይኖረውም፣ ነገር ግን የፈላስፋውን ሃሳቦች በጥራዝ ነጠቅ ለራሱ ስራወች ትክክልነት እንደማማካኛ ይጠቀም ነበር።
ኒሽ የአጻጻፉ ዘዴው እጅግ ሃይለኛና ስሜት ቀስቃሽ ነበር፣ በዚህ ምክንያት አንድ አንዶች የጀርመን ስነ ጽሁፍ አባት ይሉታል።
ኒሽ እድሜው እየጎለመሰ በሄደ ጊዜ፣ በበሽታ መሰቃየት ጀመረ። በሽታውን ለማስታገስ ከጀርመን ወደ ጣሊያን ሄዶ የተወሰነ ጊዜ ያሳልፍ ነበር። አንድ ቀን በቱሪን ከተማ ጣሊያን በመንገድ ሲዘዋወር አንድ ፈረስ በባለቤቱ በአለንጋ ሲደበደብ አይቶ ሲሮጥ ሄዶ ከፈርሱ ላይ ተጠመጠመ። ከዚያን ጊዜ ወዲህ ሙሉ በሙሉ አበደ፣ ጽሁፍም መጻፍ አቋረጠ። በዚህ ጊዜ እድሜው አርባ አመቱ ነበር። እብደቱና ከዚያም በፊት ሲያሰቃየው የነበረው በሽታ መንሴ ወይም ቂጥኝ ወይም ደግሞ የአይምሮ ነቀረሳ ነው ተብሎ በአሁኑ ጊዜ ይታመናል።
ጽሁፎቹና ስራው አሁን ድረስ ዝናን ያተረፉ፣ በዚያው ልክ የሚጠኑ ናቸው።